የስልጠና ስምምነት

አቤል በገና የዜማ መሳሪያዎች ማሰልጠኛ ማዕከል

በምዝገባ ቅጹ ላይ ከመቀበልዎ በፊት የማዕከሉን መመሪያዎች ያንብቡ።

በአቤል በገና የዜማ መሳሪያዎች ማሰልጠኛ ማዕከል በገና፣ክራር፣መሰንቆ እና ዋሽንት ለመሰልጠን የሚመጡ ተማሪዎች ሊያከብሯቸው የሚገቡ መመሪያዎች፡- 1. በተመዘገብኩበት የስልጠና ዘርፍ የሚሰጠውን ትምህርት በፍላጎት እና በአግባቡ ለመማር፣ 2. የማዕከሉን ንብረት በጥንቃቄ ልይዝና በአግባቡ ልጠቀም፣ 3. ስልጠና በሳምንት ለተመደበው የስልጠና ሰዓት በግልም ሆነ በቡድን በአግባቡ ለመሰልጠንና የሚሰጡ የስልጠና ሀላፊነቶችን ለመወጣት ፣/ቡድን የሚባለው ከአምስት ተማሪዎች በላይ ነው፡፡/ 4. ለምዝገባ ስመጣ የመመዝገቢያ 500 (አምስት መቶ ብር) ለመክፈል፣ 5. ወርሃዊ ክፍያዬን የተመዘገብኩበት ወር በገባ ቀጣይ ከ3-5 ባለት ቀናት ውስጥ መክፈል ያለብኝ መሆኑን፣ 6. በተመዘገብኩበት ሰዓት እና ቀን በመገኘት ለመማር፣ ካለ በቂ ምክንያት ላለመቅረት፣ 7. ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥመኝ የማቋረጫ ቅፅ /withdrawal form/ በመሙላት ማቋረጥ እንዳለብኝና ተመልሼ ስመጣ በማዕከሉ ለተተገበሩ አዳዲስ አሰራሮች ተገዢ ለመሆን፣ 8. ከማዕከሉ ጋር በመስማማት ከተመዘገብኩ በኋላ ትምህርቴን ባቋርጥ የከፈልኩትን ክፍያ ላለመጠየቅ፣ 9. ለስልጠና ስመጣ ስርዓቱን የጠበቀ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር የተላበሰ አለባበስ ለብሼ ለመምጣት:: 10.ማዕከሉ የሚሰጠውን ምዘና ሳልፍ የምስክር ወረቀት /certificate/ እንዲሰጠኝ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን የማዕከሉን ህግና ደንብ በማክበር ለመማር ተስማምቻለሁ፡፡